Sunday, October 14, 2012

†♥† “እግዚአብሔር ያፈቅሮሙ ለጻድቃን እግዚአብሔር የዐቅቦሙ ለፈላስያን፡፡“ (እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል፤ እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃል፡፡)“”†♥† መዝ.፻፵፭፡፰ (145፡8)



በስመ ሥላሴ
 ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ (የጸድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል።)መዝ.111፡6
ቅድመ ዓለም ዘሀሎ አለም ከመፈጠሩ በፊት ለነበረ ለእግዚአብሔር አብ እና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋን ለለበሰ ለእግዚአብሔር ወልድ እንዲሁም ከእነሱ ባለመራቅ ለሚኖር  ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፡፡ ስለ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በማብዛት አይደለም በማሳነስ በማስረዘም አይደለም በማሳጠር እንድጽፍ ያነሳሳኝ እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ጌትነትና ውዳሴ ይገባዋል አሜን በእውነት፡፡
እንኳን ለጻድቁ ለገብረ መንፈስ ቅዱስ  ዓመታዊ ክብረ በዓል፣ እንዲሁም ጴጥሮስጳውሎስ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡
እግዚአብሔር ያፈቅሮሙ ለጻድቃን እግዚአብሔር የዐቅቦሙ ለፈላስያን፡፡(እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል፤ እግዚአብሔር  ስደተኞችን ይጠብቃል፡፡)“ መዝ.፻፵፭፡፰ (145፡8)
አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሀጋራቸው ንሂሳ ግብጽ ነው፡፡ አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ፡ ይባላሉ፡፡ ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል፡፡ አንድ ቀን አቅሌሲያ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማጸን ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች፡፡ በዚሁ መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ተጸንሰው ታህሳስ 29 ተወለዱ፡፡ ዓይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ተነስተው “ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽ ልመት ውስተ ብረሃን” ብለው በማመስገናቸው ኋላም ምድራዊ መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላዕክትን ይመስላሉ፡፡
ሦስት ዓመት ሲሆናቸው ቅዱስ ገብርኤል  ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ምኔት ወስዶ ከበሩ አኖራቸው፡፡ አባ ዘመደ ብርሃን አሳድጎ አስተምሮ ከመዓርገ ምንኩስና አድርሷቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ “ሀብተ ፈውስ” ተሰቷቸዋል፡፡ በአንድ ቀን እልፍ እውራንንና አንካሳን ፈውሷል፡፡ ኋላ ግን ኤጲስ ቆጶሳቱ ካህናቱ ዝናቸውን ሰምተው እየመቱ ግብር የሚያስፈቷቸው ቢሆን ቅዱስ ገብርኤል በክንፉ ነጥቆ ከጌታ ፊት አቀረባቸው፡፡ በገድልህ በትሩፋትህ ከሞተ ነፍስ ከርደተ ገሃነም የሚድኑ ብዙ ነፍሳት አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ፡፡ ኑሮህም ከ60 አናብስተና ከ60 አናምርት ጋር ይሁን አላቸው፡፡ ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ? ብለው ጌታን ጠየቁት፡፡ “ዘኬድከ ጸበለ-እገሪከ ይልህሱ ወበውእቱ ይጸግቡ…” የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያው ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ፡፡ ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው ከአናብስትና አናምርት ጋር ይኖሩ ጀመር፡፡ ዳንኤል በአናብስት ጉድጓድ በጣለ ጊዜ አናብርቱ እንደ ድመት  ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ የረገጡትን ትቢያ ይልሱ ይታዘዟቸውም ነበር፡፡  በዚህ መልኩ መልአኩ 30 ዓመት ከቆዩ በኋላ ጌታ ባንድነት በሦስትነት ተገልጾ “ምን ላድርግልህ ትሻለህ?” አላቸው፡፡ መጀመሪያ ላሉበት መጸለይ ይገባልና የምድረ ጋቦታን ሰዎች ማርልኝ አሉት፡፡ 3000 ሃጥአንን ከሲኦል አውጥቶ ገነት አግብቶላቸዋል፡፡ “ሑር ምድረ ኢትዮጵያ ወበህየኒ ሀላውከ ነፍሳት ዘታወጽኦሙ ወደ ኢትዮጵያ ሂድ” አላቸው፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፋስ ጭኖ ምድረ ከብድ አድርሷቸዋል፡፡ ዳግመኛም ወደ ዝቋላ ደብር ቅዱስ ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጽሐ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሃጢአት አይተው ከባሕሩ በራሳቸው ቆመው ይጸልዩ ጀመር፡፡ አርባ ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ “ዘገብረ ተዝካረከ ወዘጸውዐ ስመከእምሕር ለከ ብሎሀል” አላቸው፡፡ መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ አልወጣም ብለው መቶ አመት ሲጸልዩ ኑረዋል፡፡ ከመቶ አመት በዃላ ጌታ “ተንስእ ወጻእ መሐርኩ ለከ ኩሎ ኢትዮጵያ ምሬለሃለሁ ውጣ” ብሏቸው ወጥተዋል፡፡
ከዚህ በኋላ ምድረ ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው ሰባት ዓመት እንደ ትኩል አምድ ሆነው ዓይናቸውን ሳይከድኑ ሰባት ዓመት ቆመው ጸልየዋል፡፡ ሰይጠንም በምቀኝነት ተነሳስቶ ቁራን መስሎ መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው፡፡ ሁለት ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍ ብሏቸው አድነዋቸዋል፡፡ ከዚያ ተነስተው ወደ ዝቋላ ሲሄዱ ሥላሴን በአምሳለ አረጋውያን ከጥላ ኝር አርፈው አገኟቸው፡፡ በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጽነናል አዝለህ አንድ አንድ ምዕራፍ ሸኘን አሏቸው፡፡ አዝለው ከሸኙአቸው በኋላ በአንድነት በሦስትነት ሆኖ ታያቸው ደንግጠው ወደቁ፡፡ አንስተው ዝቋላ ወርደህ ጠላቶችህን ተበቀላቸው አሏቸው፡፡በዘባነ መብረቅ ደርሰው ሰባቱን ሊቃነ መላእክት አጋዥ አርድገው እልፍ አዕላፍ አጋንንትን በማጭድ አጭደዋል፡፡ እንዲህ ለሰሚዕ እፁብ በሆነ ግብር  ዓመት በኢትዮጵያ 262 ኖረው በ562 ዓመታቸው በተስፋቸው ያመነውን በኪዳናቸው የተማጸነ ጌታ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው በዚህ ዕለት በዕለተ እሁድ ዐርፈዋል፡፡
መላእክት በአክናፈ እሳት ኢየሩሳሌም ወስደው በየማነ ምስዋዕ ቀብረዋቸዋል፡፡
ሮሜ 12፡12፣ 15፡30፣ያዕ5፡16፣ መዝ.88፡3፣111፡6 ምሳ.10፡7 ማቴ10፡40-42
 ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በቅዱስ ላሊበላ ዘመነ መንግስት መሆኑ ስለሚታወቅ ከ9- 14ኛው  ም/ዓ ድ/ል/ክ መሆኑ ነው፡፡
ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣኝ፣ ካለማወቅ ወደ መረዳት ያደረሰኝ አነሳስቶ ላስጀመረኝ አስጀምሮ ላስፈጸመኝ ጥንት ላሌለው ቀዳማዊ ፍጻሜ ላሌለው ድህራዊ ያልኖረበት ጊዜ የሌለ የማይኖርበት ጊዜም የማይኖር የዘላለም ንጉስ ሁሉን ቻይ ፈጣሪ እግዚአብሔርን በራስ ፀጉሬ ቁትር  በአጥንቶቼም ልክ አመሰግናለሁ፡፡
በሰማይ ያሉ መላእክት በምድርም የሚኖሩ የአዳም ዘር ሁሉ የሚያመሰግኗት በአማላጅነቷ ሁል ጊዜ የማትለየኝ ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበራ የብርሃን እናት የሁሉ እመቤት የአምላክ እናት ከተመረጡ የተመረጠች ከተለዩ የተለየች ከተከበሩ የተከበረች እናቴ እመቤቴ ድንግል ማርያም በቃላት ልገልጸው ከምችለው በላይ አመሰግናለሁ፡፡
ምንጭ፡- መዝገበ ታሪክ፣ ነገረ ቅዱሳን፣ የወርሃ ጥቅምት ስንክ ሳርና ገድላቸው፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ  ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡

15 comments:

  1. Egzihabher yesteln

    ReplyDelete
  2. Kale Hiwot Yasemalen bedeme betsega yetebekelen amen

    ReplyDelete
  3. It is actually a nice and useful piece of info.

    I'm glad that you shared this helpful information with us. Please stay us up to date like this. Thank you for sharing.
    Feel free to visit my blog post ; transfer rumours epl latest

    ReplyDelete
  4. I have been surfing online more than 4 hours today,
    yet I never found any interesting article like yours. It is pretty worth enough for me.
    In my view, if all site owners and bloggers made good content as you did, the web will be a
    lot more useful than ever before.

    my homepage; windows 7 gadget

    ReplyDelete
  5. Hello there! This is my 1st comment here so I just wanted to give a quick shout out and say I genuinely enjoy
    reading through your posts. Can you suggest any other blogs/websites/forums
    that go over the same topics? Thanks for your time!



    Check out my web site - Is Skin Whitening Forever a
    Scam -
    -

    ReplyDelete
  6. If you are going for fіnest contents lіke I do, just pаy a
    quick viѕit this websitе evегy ԁay since it gіves feature
    contents, thаnκs

    My ωeb page :: SICK SEO

    ReplyDelete
  7. Hey! I just want to give a huge thumbs up for the nice data
    you may have right here on this post. I might be coming again
    to your weblog for more soon.

    Also visit my weblog :: SEM

    ReplyDelete
  8. Good day! I just would like to give a huge thumbs up for the good information you��ve right here on this post.
    I might be coming back to your weblog for extra soon.


    Also visit my website SEO

    ReplyDelete
  9. You shοulԁ be willing to buy-in for 20 timeѕ the tаblе
    minimum. Gaming applications are known to occupy quite а
    huge chunk of your random access mеmory (memοrу used as
    program ωorkѕpacе). Ιn the past, there have been historiаns whо have ѕрoken out againѕt casіnos аnd there has bеen muсh сontroversy relating to thеіr еxistence anԁ uѕаgе.


    Feеl free to visit my hοmeраge spilleautomater på nett

    ReplyDelete
  10. I like to disseminate information that will I've accumulated with the yr to assist enhance group efficiency.

    Feel free to surf to my web page ... SEO

    ReplyDelete
  11. Good day! I just want to give an enormous thumbs up for the nice information you might have here on this post.
    I might be coming back to your weblog for extra soon.

    Feel free to surf to my blog post; SEO

    ReplyDelete
  12. Excellent willing synthetic eye meant for fine detail and may anticipate complications just before
    they will take place.

    Feel free to visit my homepage: SEO

    ReplyDelete
  13. You should also choose a service provider that offers simple use and excellent information security with enhanced speed and
    performance. Applications to navigate the World Wide Web until now only provided methods for deleting these files and clearing the Internet history on a category basis, or altogether.

    Transparent proxies - You'll find that a lot of open proxies are this kind of proxy.

    Feel free to surf to my site - scrapebox proxies

    ReplyDelete