Tuesday, October 23, 2012

†♥†አቡነ ዘርዓ ብሩክ†♥†



አቡነ ዘርዓ ብሩክ
አቡነ ዘርዓ ብሩክ የጻድቁ አባታችን የዘርዓ ብሩክ አባት እና እናት የተባረኩ ከቅዱሳን ወገን የሚሆኑ ነበሩ የአባታቸው ስምም ቅዱስ ደመ ክርስቶስ ሲባል እናታቸው ደግሞ ቅድስት ማርያም ሞገሳ ትባላለች ጻድቁ አባታችን ገና በናታቸው ማህጸን እያሉ ነበር ብዙ ተአምራት የሚያደርጉት እግዚአብሄር መርጡአቸዋልና በሁአላም ከክርስቶስ ልደት በሁአላ በስምንተኛው መቶ /ዘመን መጨረሻ ላይ በነሃሴ 27 ጻድቁ አባታችን ተወለዱ 40 ቀናቸውም ተጠምቀው በካህናት አፍ "ጸጋ ክርስቶስ" ተባሉ ከዛም ቤተሰቦቻቸው በጥሩ እድገት አሳደጉአቸው 7 አመትም በሞላቸው ግዜ በልጅነቴ የዚን አለም ክፋቱን እንዳላይ ብለው ቢጸልዩ አይናቸው ታውሩአል:ቤተሰቦቻቸውም የዚን አለም ትምህርት ሊያስተምሩአቸው አስተማሪ ጋር ቢወስዱአቸው ታመው ተመልሰዋል።
የእግዚአብሄር ፈቃድ አይደለምና ነገር ግን የሚያስፈልጋቸውን እውቀት ፈጣሪ አምላክ ራሱ ገልጾላቸዋል:: ክህነትን እስከ ጵጵስና እራሱ መድሃኒአለም ክርስቶስ ሰቶአቸዋል:12 አመትም በሞላቸው ግዜ አይናቸው በርቶላቸው ታላላቅ ተጋድሎን ማድረግ ጀመሩ። የሃጥያት ማሰርያን ያስሩና ይፈቱ ዘንድ ጵጵስናን በሾማቸው ጊዜ እግዚአብሄር ያወጣላቸው ሁለተኛ ስም "ዘርዓ ብሩክ" ይባል ነበር።
 3ኛውም ስማቸው ደግሞ "ጸጋ ኢየሱስ" ይባላል:: ጻድቁ አባታችን በዚህ ዓለም በህይወተ ስጋ ሳሉ አቡቀለምሲስ እንደሚባል እንደ ዮሃንስ ወልደ ነጎድጓድ እግዚአብሔር እሱ ወዳለበት ወደ ሰማይ አውጥቶ በገነት መካከል ያኖራቸው ነበር
እግዚአብሔር አምላክ ለወዳጁ ለብጹዕ አባታችን ዘርዓ ብሩክ በጎ ነገር እንዳደረገላቸውያለ ድምጽ የሰማይ ደጆችን አልፎ የእሳት ባህርን ተሻግሮ ፈራሽ በስባሽ ሲሆን እንደ ህያዋን መላእክት በፍጥነት ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ከአድማስ እስከ አድማስ ይደርስ ዘንድ 12 ክንፍን ሰጣቸው።
መላእክትም ለሌሎች ቅዱሳን ያልተሰጠ ይህንን ስልጣን አይተው ለምድራዊ ሰው ይህ ነገር እንዴት ይቻላል? እያሉ አደነቁከዛም በኋላ ጻድቁ አባታችን ከፈጣሪ ዘንድ የመላእክትን አስኬማ የሾህ አክሊል አምሳያ የሆነውን መንፈሳዊ ቆብን ሰማያዊ ቅናትን እና የደረት ልብስን (ስጋ ማርያም) ተቀብሎ በጾም እና በጸሎት በልመና እና በስግደት እግዚአብሄርን ሲያገለግል ኖረ። ከዛም በላይ ወንጌልን እጅግ ብዙ በማስተማር ደከመ።
ከኢትዮጵያም አልፎ ግብጽ ድረስ ገባ። የእስክንድርያውን ሊቀ ጳጳ አባ ዮሐንስን አገኘውና እርስ በርስ ሰላምታን ተለዋውጠው፤ እጅ ተነሳሱ።
 ከዛም ተመልሶ ወደ ሃገሩ መጣ፤ ከዛም ኢትዮጵያ ውስጥ እየተመላለሰ ወንጌልን አስተማረ እጅግ ሥጋን በሚያስጨንቅ ትጋትም የኢትዮጵያን ህዝብ ማርልኝ እያለ እያለቀሰ ይጸልይ ነበር።  
አንድ ቀን አባታችን በንጉስ ጭፍሮች ተይዘው ሲሄዱ ዳዊታቸውን ለግዮን ወንዝ አደራ ሰተዋት 5 ዓመት በሁአላ ሲመለሱ ግዮን ሆይ ዳዊቴን ግሺ መልሺሊን ቢሉአት አንድም የውሃ ጠብታ ሳይኖርባት ዳዊታቸውን ብትመልስላቸው ለደቀ መዝሙራቸው ዘሩፋኤል አሳዩትና ግዮንንም "ግሽ አባይ" ብለውታል እስካሁንም በዚሁ ስም የሚጠራው ከዚ በመነሳት ነው:: ከዚህም ሌላ ጻድቁ አባታችን በዚሁ ወንዝ አካባቢ 30 አመት ሲጸልዩ ፈጣሪ አምላክ ጸሎታቸውን ሰምቶ እጅግ ልዩ የሆነ ቃል ኪዳን ሰቶአቸዋል:በስተመጨረሻም የሚያርፉበት እለት በደረሰ ሰአት መልአከ ሞት መቶ እስኪደነግጥ እና ወደ ሁአላው እስኪያፈገፍግ ድረስ ነው ነው እግዚአብሄር ጸጋውንና ክብሩን ያበዛላቸው: በስተመጨረሻም ጥር በገባ 13 ቀን 482 አመታቸው ስጋቸው ከነፍሳቸው ተለይታ ገነትን ወርሰዋል:: ለእግዚአብሄር ምስጋና ይሁን እኛንም በኚህ ጻድቅ ጸሎት ይማረን በረከታቸውንም ያድለን አሜን!!!
ምንጭ፡ የኢትዮጵያውያን ተወላጆች ቅዱሳን ታሪክ በሊቀ ብርሃናት መርቆሬዎስ አረጋ፣ ነገረ ቅዱሳን ቁጥር ፪ በማህበረ ቅዱሳን ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ።

1 comment:

  1. I really like the composition! info
    Take a look at my web site - info

    ReplyDelete