Monday, August 20, 2012

የጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ሞት ይፋ ሆኗል መግለጫውንም እንዲህ ሰማን

" ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።"ዮሐ.1:3
PM Meles Zenawi has died. The long lasting discussion of his whereabouts are rested now. Ethiopia lost two of its powerful leaders: the premier and the patriarch. It is amazing time. May God rest their souls. Amen
ዛሬ ማለዳ ነሐሴ 15,2004ዓ/ም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ሞት ይፋ አድርጓል::

ይህንንም ተከትሎ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ Haile Mariam Desalegne named acting Prime Minister
የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሕልፈተ ሕይወት አስመልክቶ መግለጫ የሰጠው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በሙሉ ሥልጣን አገሪቱን እንደሚመሩ አስታወቀ፡፡R.I.P

የጠቅላይ ሚኒስተሩን ማረፍ እንዲህ ነበር የሰማነው ያድምጡት



በሳምንት ውስጥ ሁለት መሪ?? ወገን ይህ ብዙ ሐተታ የሚፈልግ ጉዳይ የመስላል ዋልድባንና ተመሳሳይ ጉዳዮችን ይቆየን::
" ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።"ዮሐ.1:3
እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።ሮሜ.8:28

11 comments:

  1. egziabher yewodedewun yefekedewun aderege egziabher yimesgen..........

    ReplyDelete
  2. O my God mamen Alchalkum Minyishalegnal techenku ooooooooooooooooooooooooooooo

    ReplyDelete
  3. እውነታውን ማመን ተሳነኝ ሰውነቴ እየራደ ነው አምላኬ ስለእውነት ተጨንቄያለሁ ምን ይሻለኛል ወዴት ልሂድ……

    ReplyDelete
  4. የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሕልፈተ ሕይወት አስመልክቶ መግለጫ የሰጠው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በሙሉ ሥልጣን አገሪቱን እንደሚመሩ አስታወቀ፡፡

    ReplyDelete
  5. ተጨንቄያለሁ ምን ይሻለኛል









    ReplyDelete
  6. እየሰማሁት ያለሁትን ነገር ለማመን ረዥም ሰዓት ፈጅቶብኛል፡፡ ቆይቼ ደግሞ ምናለ ውሸት በሆነ እላለሁ፡፡ አቶ መለስ ዜናዊን በዚህ ሁኔታ ማጣት አልነበረብንም፡፡ እንደ ሰው የተሳሳቷቸውን ራሳቸው አርመዋቸው፤ የጀመሯቸውን ነገሮች ውጤታቸውን አይተው፡፡ በሕይወት እያሉ ሌላ ሰው በሥልጣናቸው ተቀመምጦ፤ እርሳቸው እንደማንኛውም ሰው በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ሲራመዱ ለማየት ነበር ምኞቴ፡፡
    በተለያዩ ሚዲያዎች ስለ ሕመማቸው፣ ከዚያም ዐልፎ ስለ መሞታቸው አስቀድሞ ሲነገር ነገሩ እጅግ ያስጨንቀኝ ነበር፡፡ ከሕመማቸው ተሽሏቸው ያለፉትን ሃያ ዓመታት ስሕተቶችን ራሳቸው ያርሙታል፤ ያለፉትን ሃያ ዓመታት ጥንካሬዎችም በግለሰብ ላይ ሳይሆን በሥርዓት ላይ ይስኬዱታል ብዬ አምን ነበር፡፡
    ግን አልሆነም፡፡ ሰው መሆን አይቀርም፡፡ አሁን ራሱ ለማመን እየከበደኝም ቢሆን አቶ መለስ ዜናዊ ዐርፈዋል፡፡ ኢትዮጵያ መሪዎቿ በሕይወት እያሉ ሥልጣን ሲቀያየሩ ሳያይ፣ የመሪዎች ለውጥ የሚመጣው አንድም በሞት አንድም በስደት ብቻ እንደሆነ ልንቀጥል ነው ማለት ነው፡፡
    በአንድ ሰሞን ፓትርያርኩንና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ያጣንበት ምክንያት ምን ይሆን? የእግዚአብሔርስ መልእክቱ ምንድን ነው? ብጹዕ አቡነ ቄርሎስ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የኀዘን ቦታ ላይ ‹‹ሞት ታላቅ መጽሐፍ ነው፤ ነገርግን የሚያነበው የለም›› እንዳሉት ከሰሞኑ ሁኔታ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት፣ ሌሎቻችንስ ምን እንማራለን?
    ለሁላችንም መጽናናቱን ይስጠን፡፡አሳዛኙ ዜና http://www.danielkibret.com/2012/08/blog-post_21.html

    ReplyDelete
  7. Ene Ye waldiba yefered yimeslegnal walidba waldiba

    ReplyDelete
  8. የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ

    ReplyDelete
  9. እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ቢባል ጥሩ ነው፤ቀጣይ ምን እንደተቃጣ የሚያውቅ የለም፤የሐይማኖት አባቶች የአገር ሽማግሌዎች መንግስትን ምከሩ በዋልድባ ላይ የተቃጣው ድፍረት ንስሐ ካላስገባ የወጣው ሰይፍ ለመመለስ ከብዶኛል፤ ልቤ ፤ ነፍሴ በጣም ተጨንቄያለሁ

    ReplyDelete
  10. Every weekend i used to visit this website, for the
    reason that i want enjoyment, as this this web site conations
    in fact fastidious funny stuff too.
    Here is my site - Diamond titanium Rings

    ReplyDelete
  11. Do you mind if I quote a few of your articles
    as long as I provide credit and sources back
    to your site? My blog is in the exact same area of interest as
    yours and my visitors would really benefit from a lot of the information you provide
    here. Please let me know if this okay with you. Cheers!


    My web-site ... Louis Vuitton Purses

    ReplyDelete